ባለ ብሩህ አእምሮው ወጣት

  • Post comments:0 Comments

ሄንሪ ማርቲን የተወለደው በትሩሮ ፣ እንግሊዝ ውስጥ ሲሆን አባቱ በአንድ የንግድ ድርጅት የሂሳብ ክፍል ውስጥ ይሠራ ነበር። ማርቲን በትሩሮ የሰዋሰው ትምህርት ተማረ በኋላ፣ ለሂሳብ ትምህርት ወደ ካምብሪጅ አቀና። በታናሽ እኅቱና በቻርልስ ስምዖን አማካኝነት የወንጌል አማኝ ለመሆን ቻለ። በ1801 ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ተመረቀ፣ እንዲሁም የስሚዝ ሽልማትንም አገኘ። በዓለም ላይ ተደናቂና ተፈላጊ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ፡፡ ሁሉን እንደ ጉድፍ በመቁጠር ለታላቁ ተልዕኮ /ለሚስዮን አገልግሎት መላ ሕይወቱን፣ ከብሩን ሰጠ፡፡
“ያንን የመሰለ ጭንቅላት ይዞ እንዴት ሚስዮናዊ ይሆናል? ያለ አግባብ አንጎሉ ባከነ…” ያሉ ብዙ ሰዎች ነበሩ፡፡ ይሁን እንጂ ሚስዮናዊ ሆኖ በሄደበት በሰባት ዓመታት ውስጥ በሦስት ቋንቋዎች አዲስ ኪዳንን ተርጉሞ ለሕዝብ አበርክቶአል፡፡
ሄንሪ ማርቲን በሚስዮን አገልግሎት ልቡ እንዲነደፍ በማድግ ስሙ የሚነሣው ዴቪድ ብሬንርድ ነው። የወንጌል አደራ የውስጥ እግሩን አቃጥሎት መቆምና መቻል ያቃተው ይህ ምሁር ከእንግሊዝ ተነሥቶ ወደ ካልካታ ህንድ የ305 ቀናት ጉዞ በማድረግ ኡርዱ እና ቤንጋሊ ቋንቋን አጠና። ከ1806 እስከ 1809 በዲናፖሬ እና ከ1809 እስከ 1810 በካውንፖሬ ያለመታከት ያገለግል ነበር።
ክቡር የሆነው በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረው የሰው ልጅ ዋጋ ያልገባቸው አንዳንድ ሚስዮናዊያን በሁለቱም ቦታዎች ህንዶችን የበታች አድርጎ መመልከቱና ለህንድ ባህል ያለው ክብር ጤናማ ባለመሆኑ የርሱ ግን የተለየ በመሆኑ ብዙ እኩዮቹን አበሳጭቶና አግልሏል። ሄንሪ ማርቲን በተርጓሚዎች እርዳታ በኡርዱ፣ በአረብኛና በፋርስኛ የቅዱሳት መጻሕፍት ቅጂዎችን አዘጋጅቷል፣ በዚህም በሙስሊም ቋንቋዎች ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ አስደናቂ ሥራ ሠርቷል።

Hay, William M.; Henry Martyn (1781-1812), Fellow, Indian Missionary; St John’s College, University of Cambridge; http://www.artuk.org/artworks/henry-martyn-17811812-fellow-indian-missionary-139411

Leave a Reply